በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የተዘረጋዉ ቴክኖሎጂ ትግበራ አፈፃፀም ተገመገመ፡፡
የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ተስፋዬ መለሰ እና ክብርት ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ፍራኦል ቶለሳ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ም/ቢሮ ኋላፊዎች ለመጡት አመራሮች አቶ ነብዩ ፍቃዱ ፤ አቶ ዳኛቸዉ ፈለቀ እና የፕሮጄክት አስተባባሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዉ የተዘረጋዉን የቴክኖሎጂ ዝርጋታዉ ያለበትን አፈፃፀም ምልከታ እና ምክክር ተደርገዋል፡፡
የSD_WAN NEWORK የተዘረጋውን ኔትወርክ ወደ ስራ ለማስገባት የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሚገኝበት ሕንፃ ላይ ያሉ ተቋማት የኢንተር ኔት እና ወረዳ ኔት አገልግሎት እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎቶችን ከይግባኝ ሰሚው ጋር በማስተሳሰር በማዕከል የቴክኖሎጂ ስራዎችን የማስተዳደር ስራ እንዲሰራ ታስቦ የተዘረጋ ቢሆንም ከቴሌ ጋር በሚፈለገው ልክ ባንድዊድዝ ባለመቅረቡ እንዲሁም የG-PON መስመር ዉስንነት በመኖሩ የሚፈለገው ፍጥነት/Speed/ እና ምድብ ችሎቶችን ከመዓከል የወረፋ ማስጠበቂያ እና ሳይኔጅ ለማስተዳደር ያለዉ ክፍተቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም አማራሮች ጋር በመነጋገር ፈጣን ምላሽ ያስፈልጋል ተብለዋል፡፡
የሲስተም ልማት እና ዌብሳይትን በተመለከተ የሲስተም ልማቱን በተመለከተ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አስፈላጊዉን የማልማት ስራ ተጀመረ ቢኖርም ከሌሎች ተቃማት ጋር ያለዉን የለሙ ሲስተሞችን በፌደራል እና በሸገር ሲቲ እንዳለ በምክክሩ ወቅት በተመሳሳይ ሶፍትዌር የበልፀገ ከሆነ ወደ ተግባር ለመግባት የለሙትን ሲስተሞች ከፍርድቤቱ እና ከኢኖሎቬሽን ቢሮ አመራሮች እና ባለሞያዎች በጋራ በመሆን ምለከታ እና ተሞክሮ በመዉሰድ ተግባራዊ መደረግ አለበት ተብለዋል፡፡
በመጨረሻም የፍርድ ቤቶቹ ፕሬዝዳንቶች ለፍርድ ቤቶቹ እየተደረገ ላላው እገዛ በማመስገን ያሉን የመዛግብት ብዛት እና በተለያዩ ጊዜ ከባለጉዳዮች መረጃቸው ስለሚጠየቅ አሁን ባለን አሰራር ለብልሽት የተጋለጡ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ታግዞ ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ ባለመሆኑ እና ፍ/ቤቶቹ ወረቀት አልባ አሰራር እንዲፈጠር እንዲሁም ተገልጋይ ህብረተሰቡን ለማርካት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውና በተጨማሪም ለአይሱቲ አመራሮች እና ባለሙያዎች የግንዛቤ ፈጠራ እና የእዉቀር ሽግግር ለፍርድ ቤቱ አስፈላጊነት በንግግራቸዉ ወቅት አፅኖት ሰተዉ እንስተዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.