FAQs
Frequently Asked Questions
if you cannot find the answer below, please use the contact form or send us an email to info@example.com example@gmail.com
1.በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 327 መሠረት የሚጠየቀዉ ዳኝነት በግልጽና በአጭር ተጽፎ እና ተሟልቶ የቀረበ አቤቱታ መሆን አለበት፡፡
2.አቤቱታዉን የሚያቀርበዉ ባለጉዳይ ማንነነቱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ከተረጋገጠ በኋላ በሬጅስትራሩ ፊት በማመልከቻዉ ላይ ይፈርማል፡፡
3.የሚቀርበዉ የይግባኝ አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ ኮፒ ቀሪ እና ለመልሱ ሰጪዎች የሚደርስ በቁጥራቸዉ ልክ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4.የይግባኝ ወይም የሰበር አቤቱታ ከአራት ገጽ ያልበለጠ ሆኖ ዉሳኔ ግልባጭ ለዳኝነት የተከፈለዉን የገንዘብ መጠን ወይም ለክርክሩ የቀረበዉን ግምት የሚገልጽ የመሸኛ ደብዳቤ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
5.የይግባኝ ወይም የሰበር አቤቱታዉ የሚቀርበዉ የግለሰብ ከሆነ በቤተሰብ ዉክልና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 58 መሰረት በጠበቃ ከከሆነ ደግሞ የታደሰ የጥብቅና ፍቃድ ደብተር ከደንበኛዉ የጠሰጠዉ ህጋዊ ዉክልና እና የጥብቅና ዉል ዋናዉን እና ፎቶ ኮፒዉን መያዝ አለበት፡፡
6.የመንግስት ከሆነ አቤቱታዉን በየገጹ ላይ የተቋሙ ማህተም ተደርጎበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92/3 መሰረት የሥራ ክፍል ኃላፊዉ ማረጋገጫ በመፈረምና የሚከፍተዉ ባለሙያ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 59 መሰረት የዉክልና ማስረጃ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
7.ይግባኙ የሚቀርበዉ በአ/አ/ከ/መ/ደ/ፍ/ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ሠራተኞች አ/ር ፍ/ቤት በሰጡት ዉሳኔ ላይ ከሆነ አቤቱታዉ ዉሳኔ በተሠጠ በ60 ቀን (በሁለት ወር) ጊዜ ዉስጥ መቅረብ አለበት፡፡
8.ዉሳኔዉ የተሰጠዉ በአ/አ/ከ የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ከሆነ ደግሞ ዉሳኔዉ በተሰጠ በ30 ቀን /በአንድ ወር/ ጊዜ ዉስጥ ሆኖ የዕዳቸዉን 75 ፐርሰንት ገቢ ማድረግና ገቢ ስለማድረጋቸዉ በጽሁፍ የተደረገ ማስረጃ አያይዘዉ መቅረብ አለበት፡፡
9.የሠበር አቤቱታ የሚቀርበዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6 መሠረት በተሰጡ ዉሳኔዎች ከማህበራዊ ፍ/ቤት አልቀዉ በአ/አ/ከ/መ/ደ/ፍ/ቤት በይግባኝ በሠጠዉ ዉሳኔ እና የአ/አ/ከ/ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በሰጠዉ የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ ሲሆን ዉሳኔዉ በተሰጠ በ90 ቀን /በሶስት ወር/ ጊዜ ዉስጥ መቅረብ አለበት፡፡
10. የዳኝነት አገልግሎት ክፍያን በተመለከተ በሥር ፍ/ቤት ክርክር ላይ የተከፈለዉን የገንዘብ መጠን ግማሹ ሲሆን በትእዛዝ በወጪና ኪሳራ እንዲሁም በብይን ላይ ለሚቀርብ ይግባኝ ግን 20.00/ሃያ ብር/ በአፈጻጸም ይግባኝ ደግሞ 5.00/አምስት ብር/ ብቻ ነዉ የሚከፍለዉ ፡፡
11.ለማረጋገጫ የሚሆን መሸኛ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡ የሠበር አቤቱታ ሲሆን ይግባኙ ላይ የተከፈለዉ በድጋሚ ነዉ የሚከፈለዉ፡፡
12.በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 205 መሰረት የሚቀርብ ቃለ መሓላ በተመለከተ ከ5 ብር ቴምብር ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት ፡፡ ነገር ግን ቃለ መሃላ የሚፈጸመዉ ሰዉ በሬጅስትራር ፊት የሚፈርም ስለሆነ ተፈርሞበት አይመጣም፡፡
Ø የክስ አቤቱታ ሲቀርብ ለፍርድ ቤቱ በሁለት ኮፒ መቅረብ ያለበት ሲሆን ለተከሳሾ ች በቁጥራቸው ልክ በተጨማሪም በሲዲ ሶፍት ኮፒው መቅረብ አለበት፣
Ø የማስረጃ ዝርዝር ማስረጃዎቹም በገቢዎች ጽ/ቤት የቀረጥ ቴምብር መመታት አለበት፣
Ø ባለ ጉዳዩ ራሱ ክስ የሚከፍት ከሆነ ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
Ø በወኪል ከሆነ በፍ/ብ/ሕ ቁ. 58 መሰረት የተሰጠ ውክልና ዋና እና ኮፒ በጠበቃ ከሆነ የጥብቅና ውልና ውክልና እና የበጀት ዓመቱ የታደሰ የጥብቅና ፍቃድ ዋና እና ኮፒ፣
Ø በዐቃቢ ሕግ ወይም ነገረ ፈጅ የሚቀርብ ክስ ከሆነ አቤቱታው እና ማስረጃው የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት በኋላፊው የተፈረመ መሆን አለበት፣
Øአቤቱታ እና ቃለመሃላ በሁለት (2) ኮፒ
Øየማስረጃ ዝርዝር
Øባለጉዳዩ ራሱ አቤቱታውን የሚከፍት ከሆነ ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
Øበወኪል ከሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ.ቁ 58 መሰረት በባለጉዳዩ የተሰጠ ውክልና ዋና እና ኮፒ
Øበጠበቃ ከሆነ ከባለጉዳዮ ጋር የተደረገ የጥብቅና ውልና ውክልና እና የበጀት ዓመቱ የታደሰ የጥብቅና ፍቃድ ዋና እና ኮፒ
Øበማስረጃው ላይ የቀረጥ ቴምብር ከገቢዎች ጽ/ቤት ማስመታት፣
Øየሚቀርቡ ማስረጃዎች ከአማርኛ ቀንቋ ውጪ ሲሆን ወደ አማርኛ
Ask your Question
if you cannot find the answer below, please message us